ኮቪድ-19…

ይህ ቀጣይነት ያለው ወረርሽኝ ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዙ ምክንያቶች  ደንበኞቻችን ተመላሽ ገንዘብ ማግኘት ይችሉ እንደሆነ ብዙ ጥያቄዎች እንዲያነሱ ምክንያት ሆኗል።

ከኮቪድ-19 ጋር በተገናኘ ለተለያዩ ምክንያቶች ገንዘብ ተመላሽ እናደርጋለን፣ ስለዚህ እዚህ ላይ መክፈል ስለምንችላቸው ተመላሽ ገንዘቦች ላይ የተወሰነ ማብራሪያ ለመስጠት ሞክረናል።

ኢንፌክሽን

ቦታ አስይዘው ከመገኘትዎ በፊት ባሉት 7 ቀናት ውስጥ በኮቪድ-19 ከተያዙ፣ ይህ ማለት ራስዎን ማግለል ወይም መከልከል ከኖረቦት፤ አወንታዊ PCR የፈተና ውጤት እና/ወይም ከመንግስትዎ ራስዎን ማግለልዎን በሚያረጋግጥ ማስረጃ የተደገፈ ከሆነ። የ PCR ምርመራ ውጤት ከተጠቀሙ በተፈቀደ ላብራቶሪ ውስጥ መካሄዱ እና የተረጋገጠ የQR ወይም የባር ኮድ መያዝ አለበት።

ራስን ማግለል

በእርስዎ የቅርብ ቤተሰብ ውስጥ የሆነ ሰው በኮቪድ-19 ከተያዘ፣ ይህ ማለት እርስዎ አግባብ ባለው የብሄራዊ መንግስት ህግ መሰረት ራስዎን ማግለል ወይም መከላከያ ማድረግ ካለቦት፣ በአዎንታዊ(ፖዘቲቭ) PCR ምርመራ ወይም በመንግስት ራስን የማግለል ግንኙነት እና የአድራሻ ማረጋገጫ የተደገፈ ከሆነ።

ቀደም ሲል የነበረ የጤና ሁኔታ

ቦታ ካስይዙ በሁላ ባሉት 7 ቀናት ውስጥ ቀደም ሲል በነበረው የጤና ሁኔታዎ ላይ ከፍተኛ ለውጥ ካጋጠመዎት እና ዶክተርዎ ለኮቪድ-19 ተጋላጭ እንዳይሆኑ በመስጋት ምክንያት እንዳይገኙ ከመከሮት፣ ገንዘቡን ልንመልስልዎ እንችላለን።

ሆስፒታል መተኛት ወይም ሞት

የቅርብ ቤተሰብ የሆነ ሰው በኮቪድ-19 ምክንያት ሆስፒታል ከገባ ወይም ከሞተ፣ ቦታ ያስያዙበት ጉዳይ ከመጀመሩ በፊት ባሉት 30 ቀናት ውስጥ ከሆነ እና ማስረጃ ካሎት፣ ገንዘቡን ልንመልስልዎ እንችላለን።

መክፈል የማንችለው

በኮቪድ-19 መያዝ በመስጋት ወይም በሚኖሩበት ቤት ወይም ቤተሰብዎ ጋር ያለ አወንታዊ (ፖዘቲቭ) የኮቪድ-19 ምርመራ እራስዎን እያገለሉ ከሆነ ገንዘቡን ተመላስ ማረግ/መክፈል አንችልም።

የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመቆጣጠር በሚወሰዱ እርምጃዎች ምክንያት ለተከሰቱት የጉዞ ገደቦች/ክልከላዎች ገንዘብ ተመላሽ ማድረግ/መክፈል አንችልም።

ተመላሽ ምናረገው ገንዘብ ሁል ጊዜ ሙሉ በሙሉ በውላችን (እዚህ ሊነበብ ይችላል) መሰረት ታሳቢ ተደርጎ ነው፣ ተገቢ ማስረጃዎችን ሙሉ በሙሉ ምክንያታዊ በሆነ መልኩ እንዲቀርቡ እንፈልጋለን፣ እና ምንም አይነት ገንዘብ ተመላሽ የማድረግ ዋስትና አንሰጥም።